ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ጋር ዛሬ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ጋር በነበረን ቆይታ፣ ዘላቂ እና ተጨባጭ ለውጥ ለሚያመጣ አጋርነት መሠረት የጣለ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።
በተጨማሪም በተጨማሪም በስትራቴጂካዊ ዘርፎች ያለንን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩና የአሠራር ማዕቀፍ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የመግባቢያ ሰነዶችን ልውውጥ አካሂደናል ነው ያሉት።