የአዲስ አበባ ስኬታማ የልማት ጉዞ የዜጎችን ተጠቃሚነትና የከተማዋን ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነት እያረጋገጡ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአዲስ አበባ ስኬታማ የልማት ጉዞ የዜጎችን ተጠቃሚነትና የከተማዋን ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነት እያረጋገጡ ነው
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2018(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ስኬታማ የልማት ጉዞ የዜጎችን ተጠቃሚነትና የከተማዋን ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነት እያረጋገጡ መሆኑ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።
ከትናንት ሚያዚያ 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ሥራ አፈፃጸም ግምገማ ተጠናቋል።
በዚሁ ወቅት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ፤ በመዲናዋ ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ተሞክሮ የሚሆኑ የልማት ስኬቶች ተገኝተዋል ብለዋል።
የአዲስ አበባ የልማት ስኬቶችም ሕብረብሔራዊ አንድነትን በማፅናት በዜጎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ያመጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በኢኮኖሚ መስክም ግዙፍ ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት በመገንባት የመዲናዋን ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያንፁ ውጤታማ የልማት ስኬቶች መገኘታቸውን አስረድተዋል።
የአዲስ አባባ አስደናቂ የልማት ስኬቶች የኢትዮጵያ የብልፅግና ተምሳሌት ከተማ የመገንባት ዕሳቤን በተግባር ያስመሰከሩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
የመዲናዋ ዘርፈ ብዙ የልማት ስኬቶች የመዲናዋን ነዋሪዎች የአኗኗር ሥርዓትን በማዘመን ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ መሆኑን አንስተዋል።