የሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ የብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ሙዚየምን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ የብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ሙዚየምን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19 /2018(ኢዜአ)፦ የሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ የብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ሙዚየምን ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱ በሙዚየሙ የተደረገ ጥልቅ የታሪክ ጉዞ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት የሙዚየም ጉብኝት በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አካል እንደሆነም ጠቁሟል።
ጉብኝቱ የኢትዮጵያን ነፃና ጥንታዊ ሥልጣኔ የሚያሳይ መሆኑን የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፤ የሀገሪቱ ታሪክና ቅርሶችም ለታማኝና ባለርዕይ አጋርነቷ ህያው ምስክሮች መሆናቸውን አመልክቷል።
ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት መሆኗን የሚያሳዩ ታሪካዊ ቅርሶቿን ስታጋራ፣ ጥንታዊ ጥንካሬዋ ለዘመናዊውና ለውጥን ለሚያረጋግጠው አጋርነቷ መሠረት መሆኑን በድጋሚ ማረጋገጧን ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል።
ጉብኝቱ አፍሪካውያን ወንድሞቻችን ለጋራ የወደፊት ዕጣ-ፈንታ በአንድነት ለመሥራት ወደ ሁለተኛ ቤታቸው እንዲመጡ ጥሪ የሚቀርብበት መሆኑንም አመልክቷል።