የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ በዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኖሩ - ኢዜአ አማርኛ
የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ በዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኖሩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2018(ኢዜአ)፦ የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ በዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ የሞዛምቢክ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ በዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠው፣ ለመላው ጥቁር ሕዝቦች ነጻነት ፋና ወጊ የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች ፕሬዚዳንቱ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ስለነበራቸው ቆይታ አመስግነው፤ የሰው ዘር መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ እና የአፍሪካዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ የሰመረ እንዲሆን በራሳቸው እና በከተማ አስተዳደሩ ስም መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል።