በጋራ መከባበር ላይ ለተመሰረተ ዕድገትና ለውጥ ለሚሹ ሁሉ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ቤታቸው ናት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
በጋራ መከባበር ላይ ለተመሰረተ ዕድገትና ለውጥ ለሚሹ ሁሉ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ቤታቸው ናት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2018 (ኢዜአ)፦ በጋራ መከባበር ላይ ለተመሰረተ ዕድገትና ለውጥ ለሚሹ ሁሉ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ቤታቸው ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ወደ ኢትዮጵያ የእንኳን በደህና መጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ፣ የብዙ ጸጋዎች ባለቤት ሀገር እንደመሆኗ፤ አጋሮቿን ጸንቶ በቆየውና በጋራ መሰረቶች ላይ ማዕከል ባደረጉ የወል እድገትን ለማንበር ክንዶቿን ዘርግታ እንደምትቀበል ገልጸዋል።
አያይዘውም ከእውነተኛ አጋርነታችን የሚቀዳ፤ በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ፣ በላቀ ርዕይ የተሞላ ዕድገትንና ለውጥን ለሚሹ ሁሉ ኢትዮጵያ መድረሻ ብቻ ሳትሆን፤ ሁለተኛ ቤታቸው ናት ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ቆይታ ለጋራ ስኬትና ለዘላቂ ወዳጅነት መሠረት የሚጥል ውጤታማ እንዲሆን ተመኝተዋል።