ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ ወደ ኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ - ኢዜአ አማርኛ
ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ ወደ ኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የ24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ተካሄደዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ በአንደኝነት አጠናቋል።
አካዳሚው በሳምንቱ ያገኘውን ድል ተከትሎ አጠቃላይ የሰበሰበውን ነጥብ ወደ 51 አሳድጓል።
ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት የቀጣዩ የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተሳትፎውን ማረጋገጡን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የሚያድገው ቀሪ አንድ ክለብ በቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች የሚለይ ይሆናል።
ከከፍተኛ ሊጉ ሁለት ክለቦች ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ሲያድጉ፣ ከፕሪሚየር ሊጉ ሁለት ክለቦች ወደ ከፍተኛ ሊጉ ይወርዳሉ።