ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሞዛምቢክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ አቀባበል አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሞዛምቢክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ አቀባበል አደረጉ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2018 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሞዛምቢክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በክብር አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የፕሬዝደንቱ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የጋራ ልማትና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ትርጉም ባለው መልኩ ሊለውጡ የሚችሉ ተጨባጭ ስራዎች ቅድሚያ የሰጠ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
እንዲሁም ኢትዮጵያ ለእውነተኛ አፍሪካዊ አጋርነት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑም ተመላክቷል።