በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ይርጋጨፌ ቡና ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ይርጋጨፌ ቡና ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 18/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ይርጋጨፌ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አዳነች አስፋው በአምስተኛው ደቂቃ ግቡን አስቆጥራለች።
የይርጋጨፌ ቡናዋ ሰላማዊት ብርሃኑ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጣለች።
በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ይርጋጨፌ ቡና በ17 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል።
ላለመውረድ በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ24 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።