ቼልሲ ሊድስ ዩናይትድን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለኤፍ ኤ ካፕ ፍጻሜ ደረሰ - ኢዜአ አማርኛ
ቼልሲ ሊድስ ዩናይትድን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለኤፍ ኤ ካፕ ፍጻሜ ደረሰ
አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 18/ 2018 (ኢዜአ)፦ዛሬ በተደረገው የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ቼልሲ ሊድስ ዩናይትድን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለፍፃሜ አልፏል።
በግዙፉ ዌምብሌይ ስታዲየም በተከናወነው ጨዋታ ላይ የቼልሲን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ኤንዞ ፈርናንዴዝ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ማሸነፉን ተከትሎ በእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ከማንችስተር ሲቲ ጋር የሚጫወት ይሆናል።
ማንችስተር ሲቲ በትናንትናው እለት ሳውዝሀምፕተንን 2 ለ 1 በመርታት ለፍጻሜው ጨዋታ ማለፉ ይታወሳል።