ቀጥታ፡

በሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 3 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 18/2018 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡናን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያገናኘው ሸገር ደርቢ በቡና አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲዮም በተደረገው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና 3 ለ 1 ሲያሸንፍ ኦካይ ጁል፤ቢንያም ጌታቸው እና ዘላለም አባተ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ፍጹም ጥላሁን ነው።

ቡድኖቹ በሊጉ እርስ በእርስ ሲገናኙ የአሁኑ ለ52ኛ ጊዜ ነው።

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም