በመዲናዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተሠርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
በመዲናዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተሠርተዋል
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 18/2018 (ኢዜአ)፡- በመዲናዋ በ2018 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት የከተማዋን ነዋሪዎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች መከናወናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ሥራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው።
አቶ አደም የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ባቀረቡበት ወቅት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመዲናዋ የከተማዋን ነዋሪዎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋገጥ ከተሠሩት ሥራዎች መካከል አንዱ የሥራ ዕድል ፈጠራ መሆኑን አንስተው፤ በዚህም ከዕቅድ በላይ ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።
ዘላቂ የዕድገትና ልማት ፋይናንስ ለማረጋገጥ በቁጠባና በገቢ መሰብሰብ ላይ በተከናወኑ ተግባራት ጥሩ ውጤት መመዝገቡን ጨምረው ገልጸዋል።
በማኅበራዊ ልማት ዘርፎች በተሠራ ሥራም ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመው፤ ለአብነትም በትምህርት፣ በጤና እና በአገልግሎት አሰጣጥ ሕዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ሥራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል።
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ጥሩ ውጤት መመዝገቡን በመግለጽ፤ የትምህርት ቤት ምገባም በትምህርት ጥራት ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ነው የተናገሩት።