በሴቶች የለንደን ማራቶን ውድድር አትሌት ትዕግስት አሰፋ አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች የለንደን ማራቶን ውድድር አትሌት ትዕግስት አሰፋ አሸነፈች
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 18/2018(ኢዜአ)፦ በተጠባቂው የሴቶች ለንደን ማራቶን ውድድር አትሌት ትዕግስት አሰፋ አሸንፋለች።
በ46ኛውን የለንደን ማራቶን የሴቶች ምድብ ውድድር የፓሪስ ኦሎምፒክ የብር ሜዳልያ ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ በበላይነት አሸንፋለች።
አትሌት ትዕግስት አሰፋ ውድድሩን 2:15፡41 በሆነ ሠዓት በመግባት ነው ውድድሩን በበላይነት ጣጠናቀቀችው።
በዚሁ ውድድር ኬንያውያኑ አትሌቶች ሐለን ኦቢሪ ሁለተኛ እንዲሁም ጆይሲሊን ጄፕኮስጊ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።