ቀጥታ፡

በሲዳማ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ200 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ ገብተዋል

ሐዋሳ፤ ሚያዝያ 18/2018 (ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ200 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ መግባታቸውን የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አሻግሬ ጀንበሬ አስታወቁ።

የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሳደግ ከቦታና ኃይል አቅርቦት ባለፈ የድጋፍና ክትትል ሥራ መከናወኑን ኃላፊው ለኢዜአ ተናግረዋል።

ወደ ሥራ የገቡት አዳዲስና ነባር ኢንዱስትሪዎችም ከ20 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥረዋል ብለዋል።

የወጪና ተኪ ምርቶች በማምረት ለሀገራዊ ዕድገቱ የበኩላቸውን ሚና እያበረከቱ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

የፀሐይ ቴክ ኢንጂነሪንግና የፈርኒቸር ሥራዎች ማኔጅንግ ዳይሬክተር ተመስገን አስፋው እንደገለጹት፤ መንግሥት ባደረገላቸው ድጋፍ በአጭር ጊዜ ወደ ሥራ ገብተው ውጤታማ ሆነዋል።


 

ኤሊያና የወረቀት ማምረቻ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ደረጀ ሞገስ በበኩላቸው፤ መንግሥት የብድር፣ የመስሪያ ማሽን እንዲሁም የኃይልና የቦታ አቅርቦት ድጋፍ እንዳደረገላቸው ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም ፋብሪካው ከ150 ለሚበልጡ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም