ቀጥታ፡

ሐዋሳ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ተመራጭ የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

ሐዋሳ፤ ሚያዝያ፤ 18/2018 (ኢዜአ)፡- ሐዋሳ ከተማዋን ለሥራ፣ ለኑሮ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ተመራጭነቷን ለማስቀጠል የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ተናገሩ።

“ለሐዋሳ ከፍታ እንሮጣለን" በሚል መሪ ሐሳብ የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በሐዋሳ ከተማ ተካሂዷል።


 

የሐዋሳ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ በዚሁ ወቅት እባደረጉት ንግግር፤ ከተማዋ ታላቁ ሩጫና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ በርካታ ስፖርታዊ ሁነቶችን እያዘጋጀት ነው።

በሐዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የተመረቀውን የፀሐይ ኃይል ፓኔል ማምረቻን ጨምሮ የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችን መሳቧንም አክለዋል።

በአጠቃላይ ሐዋሳ ከተማ የታላላቅ ሁነቶችና የኢንቨስትመንት ስበት ማዕከል ሆናለችም ነው ያሉት ከንቲባው።

ከተማዋን ለሥራ፣ ለኑሮ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ተመራጭነቷን ለማስቀጠል የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም