የቼልሲ እና የሊድስ ፍልሚያ፡ ወደ ኤፍኤ ካፕ ፍጻሜ የሚያልፈው ማን ይሆን? - ኢዜአ አማርኛ
የቼልሲ እና የሊድስ ፍልሚያ፡ ወደ ኤፍኤ ካፕ ፍጻሜ የሚያልፈው ማን ይሆን?
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18/2018 (ኢዜአ)፦ በኤፍኤ ካፕ የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ይጫወታል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል።
ቼልሲ ፖርቫሌን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፉ ይታወቃል።
ተጋጣሚው ሊድስ ዩናይትድ ዌስትሃም ዩናይትድን በመርታት አራት ውስጥ ገብቷል።
ሁለቱ ክለቦች በኤፍ ካፕ ውድድር ከዚህ ቀደም ለዘጠኝ ጊዜ ተገናኝተዋል። ቼልሲ ስድስት ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል። በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
ቡድኖቹ ለመጀመሪያ ጊዜ በኤፍኤ ካፑ የተገናኙት እ.አ.አ በ1937 ሲሆን በወቅቱ በአራተኛው ዙር ተጫውተው ቼልሲ 4 ለ 0 አሸንፏል።
እ.አ.አ በ1970 በፍጻሜው ተገናኝተው ቼልሲ በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል።
ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙበት የእ.አ.አ የ2024 የአምስተኛ ዙር ጨዋታ ቼልሲ 3 ለ 2 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
ቼልሲ ለኤፍኤ ካፕ ፍጻሜ ሲያልፍ የአሁኑ ለ28ኛ ጊዜ ነው። ሊድስ ዩናይትድ ለ16ኛ ጊዜ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ ስምንት ጊዜ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን አንስቷል። ሊድስ ዩናይትድ ውድድሩን ያሸነፈው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
የዮርክሻየሩ ሊድስ ዩናይትድ ቼልሲን ለመጀመሪያ ጊዜ በኤፍኤ ካቱ ለማሸነፍ እና ለፍጻሜ ለማለፍ ይጫወታል።
የጨዋታው አሸናፊ በፍጻሜው ከማንችስተር ሲቲ ጋር ይገናኛል።
ትናንት በተደረገው የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ሳውዝሃምፕተንን 2 ለ 1 በማሸነፍ የፍጻሜውን ትኬት ቆርጧል።