ማንችስተር ሲቲ ለኤፍኤ ካፕ ፍጻሜ አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ለኤፍኤ ካፕ ፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኤፍኤ ካፕ የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ሳውዝሃምፕተንን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጄሬሚ ዶኩ እና ኒኮ ጎንዛሌዝ ለሲቲ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ፊናን አዛዝ ለሳውዝሃምፕተን ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ ለተከታታይ ዓመት ለኤፍኤ ካፕ ፍጻሜ አልፏል።
ሲቲ በፍጻሜው ከቼልሲ እና ሊድስ ዩናይትድ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።
በሻምፒዮንሺፑ የሚገኘው ሳውዝሃምፕተን ከ23 ዓመታት በኋላ ለኤፍኤ ካፕ ፍጻሜ የማለፍ ህልማቸው አልተሳካም።
የኤፍኤ ካፕ ሁለተኛ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በቼልሲ እና ሊድስ ዩናይትድ መካከል ነገ ይካሄዳል።