ቀጥታ፡

ባርሴሎና ጌታፌን በማሸነፍ ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 11 ከፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤፤ ሚያዝያ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በስፔን ላሊጋ የ33ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባርሴሎና ጌታፌን 2 ለ 0 ረትቷል።

ማምሻውን በኮሊሲየም ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፌርሚን ሎፔዝ እና ማርከስ ራሽፎርድ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በሊጉ 28ኛ ድሉን ያስመዘገበው ባርሴሎና በ85 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል። ከተከታዩ ሪያል ማድሪድ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 11 ከፍ አድርጓል።

ባርሴሎና የላሊጋውን ዋንጫ ለማንሳት ከቀሪ አምስት ጨዋታዎች የሚፈልገው ስድስት ነጥብ ብቻ ነው። 

በሊጉ 15ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ጌታፌ በ44 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሪያል ማድሪድ ትናንት ከሪያል ቤቲስ ጋር ባደረገው ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም