ቀጥታ፡

ሊቨርፑል ሲያሸንፍ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከድል ጋር ታርቋል 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 34ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መካሄዳቸውን እንደቀጠሉ ነው።

በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሊቨርፑል ክሪስታል ፓላስን 3 ለ 1 አሸንፏል።

አሌክሳንደር ኢሳቅ፣ አንዲ ሮበርተስን እና ፍሎሪያን ዊትዝ ለሊቨርፑል ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ዳንኤል ሙኖዝ ለፓላስ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል። 

ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል በ58 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ በማድረግ የአስቶንቪላን ቦታ ተረክቧል። 

ሻምፒዮንስ ሊግ ለመግባት በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል።

ክሪስታል ፓላስ በ43 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። 

በሞልኒው ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ ዎልቭስን 1 ለ 0 አሸንፏል። ጆአኦ ፓሊንሃ በ82ኛው ደቂቃ ወሳኟን ግብ አስቆጥሯል። 


 

ከ15 ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ34 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ላለመውረድ በሚያደርገው ትግል ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።  

ከሊጉ መውረዱ የተረጋገጠው ዎልቭስ በ17 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል። 

ዌስትሃም ዩናይትድ በቶማስ ሱቼክ እና ካሉም ዊልሰን ጎሎች ኤቨርተንን 2 ለ 1 አሸንፏል። ኬርናን ዴውስበሪ-ሆል ለኤቨርተን ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። 

ውጤቱን ተከትሎ ዌስትሃም ዩናይትድ በ36 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል። ከቶተንሃም ጋር ያለውን የሁለት ነጥብ ልዩነት በማስጠበቅ ላለመውረድ በሚያደርገው ትግል ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። 

ኤቨርተን በ47 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም