ቀጥታ፡

የፋብሪካዎቹ ምርቃት ሁለንተናዊ እድገት ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተመረቁት ፋብሪካዎች ዘላቂ፣ የማይበገር እና ሁለንተናዊ እድገትን ለማረጋገጥ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡትን አራት ግዙፍ ፋብሪካዎችን በይፋ መርቀዋል።


 

የተመረቁት ፋብሪካዎች የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለት፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን ያካተቱ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። 

የሶላር ፋብሪካዎቹ በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን ለገበያ ያቀርባል። 


 

ይህ ክንውን የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ለማፋጠን፣ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም ዘላቂ፣ የማይበገር እና ሁለንተናዊ እድገትን ዕውን ለማድረግ የተቀረጸውን ስትራቴጂ በማሳካት ረገድ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ እንደሚወሰድ ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም