ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ ፋብሪካዎችን መረቁ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ ፋብሪካዎችን መረቁ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ በሚገኘው የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ አራት ከፍተኛ የማምረት አቅም ያላቸው ፋብሪካዎች ዛሬ መርቀው ከፍተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙት የቶዮ ሶላር ኢነርጅ ሁለተኛው ምዕራፍ፣ ኦርጅን እና ሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካዎች መመረቃቸውን ገልጸዋል።
የሶላር መሠረተ ልማቶቹ በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋዋት ንጹህ ኃይል የሚያመነጩ ሲሆን፤ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን እንደሚያቀርቡ አመልክተዋል።
አራቱ ፕሮጀክቶች ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና የብዙዎችን ኑሮ መደገፍ መቻላቸውንና ከፍተኛ የማምረት ዐቅም ያላቸው ፋብሪካዎቹ የኢትዮጵያም እምቅ ሐብት ወደ ጥቅም የቀየሩም ሆነዋል ብለዋል።