ሲዳማ ቡና ነገሌ አርሲን በማሸነፍ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ሲዳማ ቡና ነገሌ አርሲን በማሸነፍ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 17/2018 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ዋንጫ ተጠባቂ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ነገሌ አርሲን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቤል ያለው እና ዮሴፍ ዮሐንስ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ኪቲካ ጅማ ለነገሌ አርሲ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ጨዋታውን ተመጣጣኝ ፉክክር ታይቶበታል።
ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀለ የመጨረሻው ቡድን ሆኗል።
ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን እየመራ የሚገኝ ቡድን ነው።
የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች የተጠናቀቁ ሲሆን ሲዳማ ቡና፣ ኢትዮጵያ መድን፣ መቀሌ 70 እንደርታ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ግማሽ ፍጻሜ ገብተዋል።