ቀጥታ፡

ሻምፒዮንስ ሊግ ለመግባት የሚፋለመው አስቶንቪላ በፉልሃም ሽንፈት አስተናገደ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 34ኛ ሳምንት ፉልሃም አስቶንቪላን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በክራቨን ኮቴጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራያን ሴሴኞን በ43ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። 

ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ፉልሃም በ48 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ 14ኛ ድሉን አግኝቷል።

በአንጻሩ በሊጉ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አስቶንቪላ በ58 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። 

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ እየተፎካከረ የሚገኘው አስቶንቪላ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም