በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉትን የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን ሸኝተናል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉትን የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን ሸኝተናል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉትን የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን ሸኝተናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የፕሬዝደንቱ የኢትዮጵያ ቆይታ በሁለትዮሽ የጋራ አጀንዳዎች ላይ ውይይት የተካሄደበት እና በተለያዩ ዘርፎች ስምምነት የተደረሰበት ፍሬያማ ቆይታ ነበር ብለዋል።