ቀጥታ፡

ነገሌ አርሴ እና ሲዳማ ቡና ለኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል።

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ነገሌ አርሲ ከሲዳማ ቡና በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ። 

ነገሌ አርሲ አቃቂ ክፍለ ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜ መግባቱ ይታወቃል።

ተጋጣሚው ሲዳማ ቡና በጥሎ ማለፉ አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 0 በመርታት ስምንት ውስጥ ገብቷል። 

ዘንድሮ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው ነገሌ አርሲ በ44 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሲዳማ ቡና በ54 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው።

ሁለቱ ቡድኖች በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ17ኛ ሳምንት ባደረጉት ጨዋታ ነገሌ አርሲ በዳዊት ተፈራ ጎል 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

በሊጉ ጥሩ ግስጋሴ እያደረጉ የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል።

መቀሌ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ኢትዮጵያ መድን እስከ አሁን ለግማሽ ፍጻሜ ያለፉ ክለቦች ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም