ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲት ጋር ቀጣናውን መልክ በሚያሲዙ እና የጋራ መፃኢ የልማት ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። 


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤  የሁለቱን ሀገሮች በላቀ እድገትና ተጠቃሚነት ዙሪያ መረጃ መለዋወጣቸውን ገልጸዋል፡፡


 

እንዲሁም የኢኮኖሚ ትስስርን በጠንካራ ትብብር እና በኢንቨስትመንት በመደገፍ እድሎችን የምናሰፋባቸውን የቀጣይ ስራዎች የተመለከተ ፍሬያማ ምክክር አድርገናል ሲሉም አስፍረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም