ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀብለዋል - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀብለዋል
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ከሰአት በኋላ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ ይኽ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ እና ዘላቂ ግንኙነት የሚያሳይ መሆኑን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ፤ትብብራችንን እና የጋራ ፍላጎቶቻችን ለማጠናከር የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት እንደምናደርግ እምነቴ ነውም ብለዋል።