ቀጥታ፡

በየዘርፉ የልማት ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ርዕሠ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ

ሐረር፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ የልማት ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የክልሉ ርዕሠ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

የሐረሪ ክልል መንግሥት የአስፈጻሚ አካል የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መካሄድ ጀምሯል። 


 

ርዕሠ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ግምገማው በየዘርፉ የተቀመጡ ዕቅዶችን አፈጻጸም በመፈተሽ ለቀጣይ ተግባራት ራስን ከማዘጋጀት ባለፈ  አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።

አፈፃፀሙን ከዕቅዱ አንፃር መፈተሽና ውስንነቶችን ለይቶ በቀሪ ሦስት ወራት መፈጸም ይገባል ብለዋል።

በማኅበራዊና ኢኮኖሚው ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች ስኬቶችና ተግዳሮቶችን እንዲሁም ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን መፈተሽ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ቱሪዝም፣ ኢንቨስትመንትና ሌሎች ዘርፎች ለክልሉ ኢኮኖሚ እድገት እያበረከቱ የሚገኘውን አስተዋጽዖ መመልከት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማጎልበት ሥራዎችን አጠናክሮ ከማስቀጠል አኳያም የተከናወኑ ሥራዎች እንዲሁ።

የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሠራሮችን ከማስወገድ አንጻር የተከናወኑ ተግባራትን በጥልቀት መመልከት ይገባልም ብለዋል።

ሰው ተኮር የሆኑ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም