በኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛው የግማሽ ፍጻሜ አላፊ የሚለይበት ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛው የግማሽ ፍጻሜ አላፊ የሚለይበት ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ቤንች ማጂ ቡና እና ኢትዮጵያ መድን ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ጨዋታው ከቀኑ 9 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይደረጋል።
በጥሎ ማለፉ ቤንች ማጂ ቡና ደብረ ብርሃን ከተማን በመለያ ምት በማሸነፍ ስምንት ውስጥ ገብቷል።
ኢትዮጵያ መድን ቢሾፍቱ ከተማን 2 ለ 0 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
ቤንች ማጂ ቡና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ በ27 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
የወቅቱ የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በአሁኑ በወቅት በ31 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
እስከ አሁን በተደረጉ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች መቀሌ 70 እንደርታ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል።