ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቻልን በመለያ ምት አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ አቻ በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት አምርቷል።
በዚህም ወልዋሎ 5 ለ 4 በማሸነፍ መቀሌ 70 እንደርታን ተከትሎ ግማሽ ፍጻሜ የገባ ሁለተኛ ቡድን ሆኗል።