ቀጥታ፡

መቻል እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ የግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ይጫወታሉ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል። 

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ መቻል ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሩብ ፍጻሜ ለመግባት በተደረጉ ጨዋታዎች መቻል ድሬዳዋ ከተማን፣ ወልዋሎ ንብ እግር ኳስ ክለብን ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው።

ሁለቱም ቡድኖች በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚገኙ ናቸው።

በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሊጉ ባደረጓቸው ሁለት ጨዋታዎች መቻል አንድ ጊዜ ሲያሸንፍ በቀሪው ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።

በሊጉ መቻል በ44 ነጥብ ሁለተኛ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ32 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዘዋል።

ትናንት በተደረገ የኢትዮጵያ ዋንጫ የመጀመሪያ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ ቦዲቲ ከተማን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም