ቀጥታ፡

መቀሌ 70 እንደርታ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ ቦዲቲ ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍጹም ዓለሙ፣ ፕሪንስ ኦፎሪ እና ቦና ዓሊ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።   

ሙሉቀን ተስፋዬ እና ቴዎድሮስ በለጠ ለቦዲቲ ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።  

ውጤቱን ተከትሎ መቀሌ 70 እንደርታ ግማሽ ፍጻሜ የገባ የመጀመሪያ ቡድን ሆኗል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር እስከ ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም