ቀጥታ፡

የሚበጀንን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ ወስደናል - የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች

ጎንደር፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር እድገትና ብልጽግና ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡


 

አቶ አገኘሁ አበራ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፤ ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ምርጫ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የሚኖረውን ፋይዳ በመገንዘብ ዛሬ የምርጫ ካርድ ወስደዋል።

ካርድ ያልወሰዱ የሕብረተሰብ ክፍሎችም ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ለመምረጥ ዕድሉ ሳያመልጣቸው የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ መክረዋል።

አቶ ሽፈራሁ ተስፋሁን በበኩላቸው ሳልመርጥ ቀረሁ ብሎ ከመቆጨት ይልቅ ዛሬ ካርድ በማውጣት መብትን መጠቀም የሥልጡን ማኅበረሰብ መገለጫ በመሆኑ፤ ያላወጡ ግለሰቦች ዕድሉን እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።

በሥራ መደራረብ ምክንያት የምርጫ ካርድ ሳላወጣ ብዘገይም የመጨረሻውን ቀን በመጠቀም ካርዴን እጄ ላይ አስገብቻለሁ ያሉት ደግሞ አቶ በላይ መንግሥቴ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፊታችን ግንቦት 24 ቀን 2018 . ይካሄዳል፡፡  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም