ቀጥታ፡

ምርጫ ቦርድ እስከ ዛሬ ያራዘመው የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ዴሞክራሲያዊ መብትን ለመጠቀም አስችሏል

ሐረር፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- ምርጫ ቦርድ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ያራዘመው የመራጮች የካርድ መውሰጃ ጊዜ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ ማስቻሉን የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የመራጭነት መመዝገቢያ ጊዜ ዛሬ ይጠናቀቃል።


 

የመራጭነት ካርድ ዛሬ ከወሰዱ የሐረር ነዋሪዎች መካከል አበበ አለኸኝ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት የምርጫ ካርድ ወስደው ለምርጫው ዝግጁ ሆነዋል።

ምርጫ ቦርድ ያመቻቸው ተጨማሪ የምዝገባ ቀን እንደ እኔ ላለ የተለያየ ሥራ ጫና ያለበት ሰው የመራጭነት ካርድ እንዲወስድ አስችሏል ብለዋል።


 

ዜጎች ሀገር ወዳድነታቸውን ከሚያሳዩባቸው መንገዶች አንዱ በምርጫ ንቁ ተሳታፊ መሆን ነው ያሉት ደግሞ መሠረት አባተ ናቸው።

ዛሬ የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውንና ድምጽ በሚሰጥበት ዕለት ለሀገር ይጠቅማል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።


 

መኮንን መንግሥቱ በበኩላቸው የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ጠቅሰው፤ ድምጻቸውንም ለሀገር ልማትና እድገት ይሠራል ብለው ላመኑበት ፓርቲ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም