ቀጥታ፡

የተሰጠንን ዕድል በመጠቀም የምርጫ ካርድ ወስደናል - ለመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች

ጂንካ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- የተሰጣቸውን የመጨረሻ ዕድል በመጠቀም ካርድ መውሰዳቸውን የጂንካ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ለመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ተናገሩ።


 

አቶ ዳዊት እውነቱ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል ባወጣው የምዝገባ ጊዜ አማካኝነት መመዝገብ ሳይችሉ መቆየታቸውን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመራጮች በቂ ጊዜ ለመስጠት የምዝገባ ጊዜውን በማራዘሙ ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው፤ በዚህም መሠረት ዛሬ ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል።


 

መምህርት ብርቱካን ሻኔ በበኩላቸው፤ በሥራ ጫና ምክንያት የምርጫ ካርድ አለመውሰዴ ቆጭቶኝ ነበር ብለዋል። 

አክለውም፤ ዴሞክራሲያዊ መብቴን ለመጠቀም እና የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ የመራጭነት ካርዴን በመጨረሻዋ ቀን መውሰድ በመቻሌ ደስተኛ ነኝ ነው ያሉት።


 

ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ዜጋ ሕገ-መንግሥታዊ መብቱን በመጠቀም በምርጫው መሳተፍ እንዳለበት የመከሩት ደግሞ እያሱ ሙላቱ ናቸው።

ጠቅላላ ምርጫው ዴሞክራሲያዊት ሀገር የሚገነባበት በመሆኑ ዜጎች በንቃት ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አመላክተው፤ ለዚህም ዛሬ የመጨረሻ ቀን መሆኑን አውቀው የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ መክረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም