የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ዛሬ በቦዲቲ ከተማ እና መቀሌ 70 እንደርታ መካከል ይደረጋል።
ጨዋታው ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።
በጥሎ ማለፉ ቦዲቲ ከተማ ባህር ዳር ከተማን፣ መቀሌ 70 እንደርታ ኢትዮጵያ ቡናን አሸንፈዋል።
ቦዲቲ ከተማ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ በ21 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚገኘው መቀሌ 70 እንደርታ በ29 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
የዛሬው ጨዋታ አሸናፊ ቡድን የመጀመሪያው የግማሽ ፍጻሜ አላፊ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያሉ።
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሚያሸንፍ ቡድን በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።
ውድድሩ ከ1937 ዓ.ም አንስቶ እየተካሄደ ይገኛል።