ቀጥታ፡

ቼልሲ በብራይተን ተሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 34ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ብራይተን ቼልሲን 3 ለ 0 አሸንፏል።

 

በአሜክስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፌርዲ ካዲዮግሉ፣ ጃክ ሂንሼልውድ እና ዳኒ ዌልቤክ ለብራይተን የማሸነፊያ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።


 

በጨዋታው ከፍተኛ ብልጫ የነበረው ብራይተን ተጨማሪ ጎሎችን ማስቆጠር የሚችልባቸውን እድሎች አምክኗል።

ደካማ እንቅስቃሴ ያደረገው ቼልሲ በጨዋታው ኢላማ የጠበቀ ሙከራ አላደረገም።

በሊጉ 13ኛ ድሉን ያስመዘገበው ብራይተን በ50 ነጥብ ደረጃውን ከዘጠነኛ ወደ ስድስተኛ ከፍ አድርጓል።

በአውሮፓ መድረክ ለመሳተፍ እያደረገ ባለው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቼልሲ በ48 ነጥብ ከነበረበት ስድስተኛ ደረጃ ወደ ዘጠነኛ ዝቅ ብሏል።

ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች የተሸነፈው ቼልሲ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመሳተፍ እድሉ ይበልጥ ተመናምኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም