ቀጥታ፡

የቅርስ ጥበቃ እና ልማት ለኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተው ሚና አድጓል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ለቅርስ ጥበቃና ልማት ሥራ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ዘርፉ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተው ድርሻ ማደጉን የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) ገለጹ።


 

3ኛው የቅርስ ምርምር ጉባዔ የኢትዮጵያ ቅርስ ምርምር በዲጂታል ዘመን በሚል መሪ ሐሳብ መካሄድ ጀምሯል።

ሚኒስትር ዴዔታው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የለውጡ መንግሥት በቅርስ ጥበቃና ልማት ሥራን በተመለከተ ልዩ ትኩረት በመስጠቱ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል። 


 

ቅርሶች የውጭ ምንዛሪን በማስገኘት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም ለአርኪዎሎጂስቶችና ለታሪክ ተመራማሪዎች የማይነጥፍ የመረጃ ምንጭ ሆነው እያገለገሉ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

ቅርሶች ተጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገሩ የማድረግ፣ የቅርስ አያያዝንና አጠቃቀምን የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።


 

የቅርስ ጥበቃና ልማት ሥራው ዲጂታላይዝ እየተደረገ ነው ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረ/ፕ) ናቸው።


 

ጉባዔው በቅርስ ልማት ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶችን መርምሮ መፍትሔ ለመስጠትና አዳዲስ ዕውቀቶችን ለመለዋወጥ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም