ቀጥታ፡

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 34ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ዛሬ በብራይተን እና ቼልሲ መካከል ይደረጋል።

ጨዋታው ምሽት አራት ሰዓት ላይ በአሜክስ ስታዲየም ይካሄዳል።

ብራይተን በ47 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ቼልሲ በ48 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በ33ኛው ሳምንት ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ጋር አንድ አቻ የተለያየው ብራይተን ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።

ብራይተን ካሸነፈ ተጋጣሚውን ቼልሲ በመብለጥ ስድስተኛ ደረጃን ይይዛል። 

የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ ባለፉት አራት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ተሸንፏል።

ሽንፈቶቹ ቡድኑ ሻምፒዮንስ ሊግ የመግባት ተሳትፎውን ይበልጥ እንዲጠብ አድርገዋል።

ቼልሲ በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ ህልሙን እውን ለማድረግ ጨዋታውን የግድ ማሸነፍ ይጠበቅበታል።


 

በኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የሚጫወቱት ማንችስተር ሲቲ፣ ቼልሲ እና ሊድስ ዩናይትድ የ34ኛ ሳምንት ጨዋታቸውን አስቀድመው ያደርጋሉ። 

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 34ኛ ሳምንት እስከ ሚያዚያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም