ቀጥታ፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ ጋር ይጫወታል 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል።

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። 

ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድር ዓመቱ 26 ጨዋታዎችን አድርጎ በስምንቱ ሲያሸንፍ በ10ሩ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪ ስምንት ጨዋታዎች አቻ ወጥቷል።

በ26ቱ ጨዋታዎች 22 ግቦችን ሲያስቆጥር 24 ጎሎችን አስተናግዷል።

አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ32 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል። 

በሊጉ ካከናወናቸው 27 ጨዋታዎች መካከል ሰባቱን ያሸነፈው አዳማ ከተማ በበኩሉ ስምንት ጊዜ ተሸንፎ በ12 ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቷል።

ባደረጋቸው ጨዋታዎችም 24 ግቦችን ሲያስቆጥር 28 ጎሎች ተቆጥረውበታል።

አዳማ ከተማ በ33 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 

በ27ኛ ሳምንት ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ሁለት አቻ የተለያየው ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል። 

ባለፉት ሰባት የሊጉ ጨዋታዎች ከድል የራቀው አዳማ ከተማ ማሸነፍ ወደ ድል መንገድ ይመልሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም