ክሪስታል ፓላስ እና ዌስትሃም ዩናይትድ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ክሪስታል ፓላስ እና ዌስትሃም ዩናይትድ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ክሪስታል ፓላስ እና ዌስትሃም ዩናይትድ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ትናንት ማምሻውን በሰልኸርስት ፓርክ በተካሄደው ጨዋታ ዌስትሃም ከተጋጣሚው የተሻሉ የግብ እድሎችን ቢፈጥርም ወደ ግብ መቀየር አልቻለም።
ባለሜዳው ክሪስታል ፓላስ አንጻራዊ የኳስ ቁጥጥር ብልጫውን ወደ ጎል እድሎች በሚገባ መቀየር አልቻለም።
ውጤቱን ተከትሎ ክሪስታል ፓላስ በ43 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል።
ዌስትሃም ዩናይትድ በ33 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ከመውረድ ስጋቱ አልተላቀቀም።
የአቻ ውጤቱን ተከትሎ በ17 ነጥብ 20ኛ ደረጃን የያዘው ዎልቭስ አምስት ጨዋታዎች እየቀሩት ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱ ተረጋግጧል።
የ33ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል።
የ34ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል።