ቀጥታ፡

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከኦስትሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2018 (ኢዜአ)፡- የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከኦስትሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቤይት ሜንለ-ሪዝንገርን ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያና ኦስትሪያ የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ታሪካዊ የዲፕሎማሲና ቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ መክረዋል።


 

ውይይቱን አስመልክቶ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓና የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ለኢዜአ በሰጡት ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያና ኦስትሪያ ዘመናትን የተሻገረ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ብለዋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከኦስትሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቤአተ ማይነል-ረይዚንገር ጋር በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ትብብር ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል።


 

በውይይቱም ፕሬዝዳንት ታዬ በኢትዮ-ኦስትሪያ መካከል የካበተ ታሪክ ያለው ወዳጅነት መኖሩን መግለጻቸውን አንስተዋል።

የሀገራቱ ታሪካዊ መልካም ግንኙነትም በዘርፈ ብዙ የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸዋል።

የኦስትሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቤአተ ማይነል-ረይዚንገር በበኩላቸው፤ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ የዲፕሎማሲ ወዳጅነት የበለጠ ለማጠናከር እንደምትሰራ ገልጸዋል ብለዋል።


 

የኢትዮ-ኦስትሪያን ከ120 ዓመታት በላይ የተሻገረ ታሪካዊ ስትራቴጂክ አጋርነትም በህዝብ ለህዝብ እንዲሁም ጸጥታ ጉዳዮች ለማጠናከር እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።

የጉብኝታቸው ዓላማም ከ120 ዓመታት በላይ የተሻገረውን የዲፕሎማሲ ትብብር በሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን የበለጠ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ማንሳታቸውንም ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም