ሸገር ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ሸገር ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ሸገር ከተማ ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቢንያም ፍቅሩ እና ቡልቻ ሹራ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ከሶስት የሊግ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሸገር ከተማ በ35 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ ያሸነፋቸው ጨዋታዎች ብዛት ሰባት ደርሰዋል።
በአንጻሩ በሊጉ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በ36 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።
ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፈም።