በመደመር እሳቤ የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠል የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ኢዜአ አማርኛ
በመደመር እሳቤ የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠል የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
ቡታጅራ ፤ሚያዝያ 12/2018(ኢዜአ)፦በለውጡ ዓመታት በመደመር እሳቤ የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠል የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ።
በለውጡ ዓመታት በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ለተመዘገቡ ስኬቶች እውቅና የሚሰጥ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በቡታጅራ ከተማ ተካሂዷል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በለውጡ ዓመታት የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ባስቀደመ መንገድ በተለያዩ ዘርፎች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተግባራትን በማከናወን ስኬቶች ተመዝግበዋል።
በመደመር እሳቤ የተገኙ እነዚህን ስኬቶችን በማስቀጠል የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ታምርትና ሌሎች ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በተከናወኑ ሥራዎች ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
በየዘርፉ የህዝብን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግም ለዲጂታል አሰራርና ለወል ትርክት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በበኩላቸው፥ የብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በፖለቲካ ፣በማህበራዊና በኢኮኖሚው መስክ በርካታ ስኬቶች ማስመዝገቡን አንስተዋል፡፡
በዞኑ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሌማት ትሩፋት እና የኢንዱስትሪ ልማት ሥራዎች በቅንጅት መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡