ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 29ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 12/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 29ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል።

እስከ ነገ ድረስ በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ላይ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተደርጎበት ጸድቋል።

ጉባኤው የውጭ ኦዲተርን የመሰየም እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲት ሪፖርትን በማዳመጥ ተወያይቶ የማጽደቅ አጀንዳዎችን ይዟል።


 

በተጨማሪም የ2018 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድና በጀት ላይ በመምከር ውሳኔ የሚያሳልፍ ይሆናል።

ሌላው በጉባኤው የሚዳሰሰው ጉዳይ ተቋማዊ አሰራር (ሪፎርም) ሰነድ እና የሰው ኃይል መዋቅራዊ ጥናትን ተመልክቶ ማጽደቅ ሲሆን፣ የተሻሻለውን የፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብም መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ጉባኤው የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድን እንዲሁም የተሻሻለውን የፌዴሬሽኑ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር መመሪያን በአጀንዳነት በመያዝ ውይይት በማድረግ እንደሚያጸድቅ የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም