ቀጥታ፡

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ዛሬ በክሪስታል ፓላስ እና ዌስትሃም ዩናይትድ መካከል ይካሄዳል። 

ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሰልኸረስት ፓርክ ስታዲየም ይካሄዳል።

ክሪስታል ፓላስ በ42 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። ዌስትሃም ዩናይትድ በ32 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 

ሁለቱ ክለቦች በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሲገናኙ የአሁኑ ለ35ኛ ጊዜ ነው።

ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 34 ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ በ13ቱ ሲያሸንፍ ዌስትሃም በ11ዱ ድል ቀንቶታል። በቀሪ 10 ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተዋል። 

በ34ቱ ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ 52 ግቦችን ሲያስቆጥር፣ ዌስትሃም ዩናይትድ 50 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ቡድኖቹ ባለፉት አምስት የሊግ ግንኙነታቸው ፓላስ ሶስት ጊዜ ሲያሸንፍ ዌስትሃም አንድ ጊዜ ድል ቀንቶታል። በቀሪ አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።

በዘንድሮው የውድድር ዓመት በአምስተኛ ሳምንት በለንደን ስታዲየም ተገናኝተው  ክሪስታል ፓላስ 2 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

በ32ኛ ሳምንት ኒውካስትል ዩናይትድን 2 ለ 1 ያሸነፈው ክሪስታል ፓላስ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል።

በተመሳሳይ በ32ኛ ሳምንት ዎልቭስን 4 ለ 0 የረታው ዌስትሃም ዩናይትድ ከወራጅ ቀጠናው ለመራቅ ሶስት ነጥብ ማግኘት ወሳኝ ነው።

ሁለቱ የለንደን ክለቦች በጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ያሳያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም