የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።
ከቀኑ 10 ሰዓት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ መድን በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ41 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። ኢትዮጵያ መድን በ30 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በ27ኛ ሳምንት አዳማ ከተማን 1 ለ 0 ያሸነፈው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በድል ጉዞው ለመቀጠል ይጫወታል።
የወቅቱ የሊጉ የዋንጫ ባለቤት ኢትዮጵያ መድን ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።
መድን ማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት የሚያስችለውን ወሳኝ ሶስት ነጥብ ያስገኝለታል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ከሸገር ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ባህር ዳር ከተማ በ36 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። ሸገር ከተማ በ32 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በ27ኛ ሳምንት ከኢትዮጵያ መድን አንድ አቻ የተለያየው ባህር ዳር ከተማ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።
ባህር ዳር ከተማ በሊጉ በበርካታ ጨዋታዎች (15 ጊዜ) አቻ የወጣ ቡድን ነው።
ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ያላሸነፈው አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ ሶስት ነጥብ ከወራጅ ቀጠና አካባቢ እንዲርቅ ያስችለዋል።
ምድረ ገነት ሽሬ ከወላይታ ድቻ ከቀኑ 10 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ምድረ ገነት ሽሬ በ29 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ወላይታ ድቻ በ31 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።
ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ምድረ ገነት ሽሬ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት በሚያደርገው ትግል ሶስት ነጥብ ማግኘት ግድ ይለዋል።
በ27ኛ ሳምንት በፋሲል ከነማ 1 ለ 0 የተሸነፈው ወላይታ ድቻ ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ ይጫወታል።