ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ያጠናከረበት ወሳኝ ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ያጠናከረበት ወሳኝ ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አቤል ያለው ግቦቹን አስቆጥሯል።
በሊጉ 15ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሲዳማ ቡና በ54 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።
ከተከታዩ መቻል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 10 ከፍ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ32 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል።
የሲዳማ ቡናው አቤል ያለው በሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ወደ 14 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት መሪነቱን አጠናክሯል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር መቻል እና ሃዋሳ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
መቻል በ44 ነጥብ ሁለተኛ፣ ሃዋሳ ከተማ በ43 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ነገሌ አርሲ ከሀድያ ሆሳዕና አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኪቲካ ጅማ ለነገሌ አርሲ፣ ተመስገን ብርሃኑ ለሀድያ ሆሳዕና ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ነገሌ አርሲ በ44 ነጥብ ሶስተኛ፣ ሀድያ ሆሳዕና በ34 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም አስቀድሞ የተካሄደው የኢትዮጵያ ቡና እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ቢንያም ጌታቸው ለኢትዮጵያ ቡና፣ ይድነቃቸው ያሲን ለአርባምንጭ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ኢትዮጵያ ቡና በ38 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
አርባምንጭ ከተማ በ24 ነጥብ የመጨረሻው 20ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።