ቀጥታ፡

ባየር ሙኒክ የቡንድስሊጋ ዋንጫን ለ35ኛ ጊዜ ማንሳቱን አረጋገጠ 

አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- በጀርመን ቡንድስሊጋ 30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባየር ሙኒክ ስቱትጋርትን 4 ለ 2 አሸንፏል።

ማምሻውን በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሃሪ ኬን፣ ኒኮላስ ጃክሰን፣ አልፎንሶ ዴቪስ እና ራፋኤል ጉሬሮ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ቼማ አንድሬስ እና ክሪስ ፉህሪች ለስቱትጋርት ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።


 

በሊጉ 25ኛ ድሉን ያስመዘገበው ባየር ሙኒክ አራት ጨዋታ እየቀረው የቡንደስሊጋ ዋንጫን ማንሳቱን አረጋግጧል።

ለ35ኛ ጊዜ ጊዜ ቡንድስሊጋውን በማሸነፍ የጀርመን የበላይነቱን አስመስክሯል።

ሙኒክ ካለፉት 15 የቡንድስሊጋ ዋንጫዎች 14ቱን አንስቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም