ቀጥታ፡

ሊቨርፑል፣ ኖቲንግሃም ፎረስት እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- በ33ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።

በመርሲሳይድ ደርቢ ከኤቨርተን ጋር ጨዋታውን ያደረገው ሊቨርፑል 2 ለ 1 ሲያሸንፍ፤ ሞሀመድ ሳላህ እና ቨርጂል ቫንዳይክ ለሊቨርፑል እንዲሁም ቤቶ ለኤቨርተን ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡


 

በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር በቪላ ፓርክ ስታዲየም ሰንደርላንድን ያስተናገደው አስቶን ቪላ 4 ለ 3 ረትቷል።

በዚህ ጨዋታ ኦሌ ዋትኪንስ (2)፣ ሞርጋን ሮጀርስ እና ታሚ አብርሃም ለአስቶንቪላ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።


 

እንዲሁም ክሪስ ሪግ፣ ትራይ ሀም እና ዊልሰን ኢስዶር የሰንደርላንድን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

ኖቲንግሃም ፎረስት ደግሞ በርንሌይን 4 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም