ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳንን 6 ለ 0 አሸነፈች

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ለ2026 ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳንን 6 ለ 0 አሸንፋለች።

ጨዋታው ዛሬ 10 ሠዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሂዷል።

ግቦቹን ያስቆጠሩትም፤ ሲርያ ተሾመ፣ ምኅረት አየለ (3) እንዲሁም ሊያን ዳንኤል (2) ናቸው።

በድምር ውጤትም ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳንን 8 ለ0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ረትታለች።

ውጤቱን ተከትሎም ኢትዮጵያ በቀጣይ ከቡርንዲ ጋር እንደምትጫዎት የወጣው መርሐ ግ-ብር ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም